በዘር የሚተላለፍ የኮሌስትሮል ህመም (የፋሚሊያል ሃይፐርኮሌስትሮሌሚያ, Familial Hypercholesterolemia, FH) በጣም ከፍተኛ የኮሌስትሮል መብዛት የሚያመጣና ለልብ ህመም የሚያጋልጥ የተለመደ በዘር የሚወረስ በሽታ ነው።

በአለም አቀፍ ደረጃ ከ300 ሰዎች አንዱን እንደሚያጠቃ የተረጋገጠ ሲሆን በዘር ከሚወረሱ የሜታቦሊክ ህመሞች በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው። በሃገራችን ኢትዮጵያም ይህ በሽታ እንዳለ ማረጋገጫዎች ቢኖሩም የህመሙን ስፋት ከ100 ሺህ በላይ ሰዎችን ሊይዝ እንደሚችል ከመገመት ውጭ በውል አይታዎቅም።

ነገር ግን ይህን ህመም አስቀድሞ ማወቅ ሕይወትን ከከፋ የልብ ህመም የሚታደግ ነው። የዚህ የኮሌስትሮል ህመም ተጠቂዎች በጊዜ አስፈላጊውን ምርመራ እና ህክምና ያገኙ ዘንድ መቼ ነው ወደ ህመሙን መጠርጠር እና የኮሌስትሮል ስፔሻሊስት ሪፈር መደረግ ያለብን?

ከዚህ እንደሚከተለው በጣም ከፍ ያለ በተለይም ኮሌስትሮል አምጭ ግልጽ ምክንያቶች (secondary dyslipidemia) ከሌለ በዘር የሚተላለፍ የኮሌስትሮል ህመም ሊሆን ስለሚችል መለየትና በጊዜ ሪፈር ማድረግ ይመከራል።

  • Total cholesterol >300 mg/dl
  • LDL-C >200 mg/dl
  • በህክምና ሊስተካከል ያልቻለ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መብዛት
  • በቆዳና ጅማት ላይ የሚወጡ ቢጫማ እብጠቶች (xanthoma) ዋነኛ የህመሙ ምልክቶች ናቸው። እነዚህ እባጮች በቁርጭምጭሚት አካባቢ የተረከዝ ጅማት (ቋንጃ) ላይ፣ በጉልበት፣ በእጆች ወይም ክርን ላይ ሊወጡ ይችላሉ። በአይን ዙሪያም (xanthelasma) ሊወጡ ይችላሉ። እነዚህ እብጠቶች በቀላሉ የሚታዩ ቀለማቸው ቢጫማ ሲሆን ኮሌስትሮል በቆዳና ጅማት ውስጥ ሲከማች የሚመጡ ናቸው።
  • የአይን መስታውት ዙሪያ ላይ የሚወጣ ቀለበቶች (arcus cornealis) ሌላኛው የኮሌስትሮል ህመም መገለጫ ሊሆን ይችላል። ይህ ነጭ ወይም ግራጫ ቀለም ያለው ክብ መሰል ሲሆን ኮሌስትሮል በአይን መስታወት ዳርቻ ላይ ሲከማች የሚፈጠር ነው። በአብዛኛው በአረጋውያን ላይ ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚታይ ሲሆን ከ45 ዓመት በታች በሆኑ ሰዎች ላይ ሲታይ የኮሌስትሮል ህመም ምልክት ነው።
  • ከቤተሰብ አባላት ውስጥ በወጣትነታቸው ከ50 አመት እድሜ በፊት ድንገተኛ የልብ ድካም (heart attack) ወይም ስትሮክ (stroke) ያጋጠመው ካለም እንዲሁ የዚህ የኮሌስትሮል ህመም ምልክት ሊሆን ይችላል።

እንደዚህ በጣም ከፍ ያለ የኮሌስትሮል ምርመራ ውጤት ያላቸውን ሰዎች ቶሎ ወደ ስፔሻሊስት የኮሌስትሮል ሃኪም ሪፈር በማድረግ ለሕይወት አስጊ የሆኑ የጤና ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል ወሳኝ ነው።

ተጨማሪ ጥያቄዎች ወይም ግብረ መልስ ካሉዎት የዚህን መረጃ ያሰናዳዉን ዶ/ር መላኩ ታዬ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የስኳር ህክምና ክፍል ማግኘት ይችላሉ።

ተጨማሪ ተግባራዊ ምክሮችን በዶ/ር መላኩ ድህረ ገጽ www.melakutaye.com እና ማህበራዊ ሚዲያዎች @hakimmelaku ይከታተሉ!

telegram https://t.me/hakimmelaku

write me feedback at https://maps.app.goo.gl/twmS9fq7LiG1eRnq9

WhatsApp +251921720381

Dr. Melaku Taye (Endocrinologist, Lipidologist)

Get social with Hakim on Youtube: http://www.youtube.com/@Hakim207

@HakimEthio

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *