በፊንጢጣዎ ውስጥ ያበጡ ደም መላሽ የደም 🩸 ስሮች ሄሞሮይድስ ይባላሉ።

  • ውስጣዊ ሄሞሮይድስ በፊንጢጣ ወይም በታችኛው የኩስቋት ውስጥ ይከሰታል። አንዳንዴ ከፊንጢጣ ውጭ ሊያድጉ እና ሊወጠሩ ይችላሉ።
  • ውጫዊ ሄሞሮይድስ በፊንጢጣ አካባቢ ባለው ቆዳ ላይ ይከሰታል።

ትክክለኛው መንስኤ ምን እንደሆነ ባይታወቅም፤ አስተዋፅዖ ያላቸው ምክንያቶች በፊንጢጣ ውስጥ ባሉት የደም ቧንቧዎች ላይ ጫና እንደሚፈጥሩ ይታመናል። የሆድ ድርቀት እና እርግዝና የፊንጢጣ ግፊት መጨመር ሊያስከትል ይችላል።


የሄሞሮይድስ ምልክቶች ምንድ ናቸው? 🙋‍♀️

ውስጣዊ ሄሞሮይድስ አብዛኛውን ጊዜ ህመም የለውም። ነገር ግን ሲታዩ ምልክቶቹ የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

  • በፊንጢጣ አካባቢ የቆዳ ማሳከክ
  • ደም መፍሰስ – ብዙውን ጊዜ ህመም የሌለው ሽንት ቤት ከተጠቀሙ በኋላ ደማቅ ቀይ ደም ሊያዩ ይችላሉ።
  • ህመም – በሄሞሮይድ ውስጥ የደም መርጋት ከተፈጠረ ህመም ሊያስከትል ይችላል። እንዲሁም በፊንጢጣ ውስጥ የመሞላት ስሜት ያለው እብጠት ሊያስከትል ይችላል።

ውጫዊ ሄሞሮይድስ ማሳከክ እና ህመም ሊያስከትል ይችላል። አንዳንድ ጊዜ በፊንጢጣ ጠርዝ ላይ በጣም የሚያሠቃይ ሰማያዊ/ሐምራዊ እብጠት ሊሆን ይችላል።


ዶክተርዎን መቼ ማየት አለብዎት? 🙋‍♂️

  • ደም እየፈሰሱ ከሆነ ሐኪምዎን ማማከር አስፈላጊ ነው።
  • በፊንጢጣ አካባቢ ላይ ከፍተኛ የሆነ ህመም ካጋጠመህ ይህ በትንሽ የቀዶ ጥገና ሂደት ሊፈታ የሚችል የውጪ ሄሞሮይድ ምልክት ሊሆን ይችላል።

ሄሞሮይድስ እንዳይከሰትብኝ ምን ማድረግ አለብኝ? 💡

በጣም አስፈላጊው ነገር የሆድ ድርቀትን መከላከል ነው።

  • ▶️ ብዙ ትኩስ ፍራፍሬ፣ ጥሬ ወይም የበሰለ አትክልት እና ሙሉ እህል በመመገብ ፋይበር ይጨምሩ።
  • ▶️ አልኮል ያልሆኑ ፈሳሾች በብዛት ይጠጡ።
  • ▶️ አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ።
  • ▶️ ሰገራ ፍላጎት ሲሰማ ወዲያውኑ ሽንት ቤቱን ይጎብኙ። መጠበቅ ድርቀት ሊያስከትል ይችላል።

🤕 ህመሙን እንዴት ማስታገስ ይቻላል?

ከሚከተሉት ውስጥ ጥቂቶቹ የህመም ማስታገሻ እርምጃዎች ሊረዱ ይችላሉ፦

  1. በቀን 3 ጊዜ እና ሽንት ቤት ከገቡ በኋላ ከ8–10 ሴ.ሜ የሞቀ ውሃ ላይ ተቀምጠው ይዘፍዘፉ።
  2. ለ10 ደቂቃዎች በቀን ብዙ ጊዜ በፊንጢጣ አካባቢ በረዶ ያድርጉ፤ በኋላ ሙቅ እና እርጥብ ፎጣ ይጨምሩ።
  3. የህመም ማስታገሻ መድሃኒት እንደታዘዘው ይውሰዱ።
  4. የፊንጢጣ ክፍል ንፁህ ያድርጉት።
  5. ከጥጥ የተሰራ የውስጥ ሱሪ እና የለሰለሱ ልብሶች ይልበሱ።
  6. ተጨማሪ ፋይበር ይበሉ።
  7. ብዙ ፈሳሽ ይጠጡ።
  8. ፍላጎት ሲሰማ በወቅቱ ሽንት ቤት ተጠቀም።
  9. ሰገራ ለማለፍ መወጠርን ያስወግዱ።

🤕 ሄሞሮይድስ ባይፈወስስ?

ስለ አማራጮችዎ ከቀዶ ሀኪምዎ ጋር ይነጋገሩ። ዶክተርዎ ሄሞሮይድስን ለማከም በቢሮ ላይ ወይም በቀዶ ጥገና ሊያደርግ ይችላል።


ምንጭ፡ uptodate, Shwartz, world society of emergency surgery, American acadamy of family physician

👨‍⚕️ ዶ/ር አለምነህ ምትኩ ፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፣ የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ሀኪም

📞 0930005416
🌐 📱 Telegram

@HakimEthio

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *