የጡት ካንሰር በአንዱ ወይም በሁለቱም ጡት ላይ የሚጀምር የካንሰር አይነት ነዉ ።አብዛኛው የበሽታው ተጠቂዎች ሴቶች ቢሆኑም ወንዶችንም ሊይዝ ይችላል።
ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች
የጡት ካንሰር ተጋላጭነትን ከሚጨምሩ ነገሮች መካከል አልኮል መጠጥን አዘውትሮ መጠጣት፣ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ልጅ አለመውለድ ወይም ከ 30 አመት በኋላ መውለድ፣የእርግዝና መከላከያዎች እና የድህረ ማረጥ ሆርሞናል ህክምናዎች በዋናነት ይጠቀሳሉ።
ምልክቶች
የጡት ካንሰር ዋነኛው ምልክት በጡት ውስጥ አዲስ እባጭ ወይም መጓጎል ነው።ይህ እባጭ በአብዛኛው ህመም አልባ እና ጠንካራ ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ ለስላሳ እና ህመም ያለው ሊሆን ይችላል።ሌሎች ምልክቶች:- ጡት አካባቢ ባለ ቆዳ ላይ ሰርጎድ ማለት (አንዳንዴም ቀለም እየቀየረ)፣የጡት ወይም የጡት ጫፍ ህመም፣የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መግባት፣ከጡት ጫፍ ፈሳሽ መውጣት እና በብብት ስር እንዲሁም ደረት ጫፍ ላይ ያሉ የንፍፊቶች እብጠት ናቸው።
ምርመራ
የጡት ካንሰር ምርመራ በዋናነት የሚካሄደው በማሞግራም ነው።ይህ ዘዴ የጡት ውስጣዊ ክፍልን ይመረምራል። በሽታው የሚጀምረው በጡት ውስጥ ከሚከሰት እባጭ ስለሆነ ማንኛውም አይነት እብጠት ወይም መጓጎል በጡት ውስጥ ካጋጠመ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ምርመራ ማድረግ ይመከራል።
ህክምና
የህክምና አማራጮች ሰፊ ቢሆኑም ጥቅማቸው ካንሰሩ እንዳለበት ደረጃ ይወሰናል።ሁለት አይነት የ ቀዶ ጥገና አይነቶች ሲኖሩ ላምፔክቶሚ(ካንሰር ያጠቃውን የጡት ክፍል ብቻ ማስወገድ) እና ማስቴክቶሚ(ጡትን በጠቅላላ ማስወገድ) ይሰኛሉ።ሌሎችም የሆርሞን፣የጨረር እና ኬሞቴራፒ አማራጮች እንዳለበት ደረጃ እና ሁኔታዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ።
ለበለጠ መረጃ ድህረ ገፃችንን ይጎብኙ mirkuz.org
ይደውሉልን : 0946617007
@mirkuz2023