በኦፕሬሽን መውለድ (Caesarean section) – ማለት ከ28 ሳምንት በውሀላ ማደንዘዣ ተሰጥቶ ልጅሽ እና ከልጅሽ ጋር አብሮት የነበረው የእንግዴ ልጅ በሆድሽ በታችኛው ክፍል ላይ በሚደረግ ትንሽ መቅደድ ልጅሽን ከማህፀን የማውጣት ወይንም የማስወለድ መንገድ ነው።
በኦፕሬሽን መውለድ (Caesarean section) – በድንገተኛ ሁኔታ (Emergency CS) ወይም ደግሞ ለእናቲቱ ቀን ተቆርጦላት (Elective CS) ሊሰራላት ይችላል።
አንዲት እናት በC/S እንድትወልድ ሊያረጓት የሚችሉ ነገሮች ብዙ ቢሆንም ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው:-
በእናቲቱ ምክንያት
- በፊት ኦፕሬሽን መኖር
- የማህፀን ጥበት
- የእንግዴ ልጅ መድማት
- የእንግዴ ልጅ ቀድሞ መምጣት
- የምጥ መድሀኒት ተሞክሮ አለመሳካት
- የልብ, የአተነፋፈስ እና የመሳሰሉት ችግር ካለባት
- ፅንሱን የሚከለክል እጢ ካለ ወይም የማህፀን ጫፍ ካንሰር ወዘተ…
በፅንሱ ምክንያት
- ፅንሱ ከታፈነ
- መንታ ሆኖ የመጀመሪያው ልጅ በጭንቅላቱ ካልመጣ (በጎን ወይም በቂጡ ከሆነ)
- ከሁለት በላይ ፅንስ ካለ
- እትብት በድንገት ከወጣ
- የፅንሱ ኪሎ ከ4.5 kg ለስኳር በሽተኞች እና 5 kg ለጤናማ እናት በላይ ሲሆን (በኛ ሀገር ፅንሱ ከ4 kg በላይ ከሆነ ትልቅ ይባላል፤ ለዛም በምጥ ማምጫ በማህፀን እንድትወልድ አይመከርም
- ፅንሱ አመጣጡ ላይ ችግር ካለ (በጎን ከመጣ፣ በእግሩ ከመጣ፣ ጭንቅላቱ በሚፈለገው መንገድ ሆኖ ካልመጣ) ወዘተ…
የኦፕሬሽን የጎንዮሽ ችግር
በኦፕሬሽን ጊዜ
- የማህፀን ቅድ ልጅ ሲወጣ መለጠጥ እና ቅዱ በመጨመር ያልተፈለገ አደጋ ማምጣት፣ የማህፀን ቧንቧ እና ወደ ፊኛ የሚወስድ የሽንት ቧንቧ መጎዳት፣
- ልጅ ከወጣ በውሀላ ማህፀን ጠንክራ ደም ማቆም ሲገባት በጣም ስስ መሆን እና ደም አልቆም ማለት
- ከሚሰጣት የማደንዘዣ መድሀኒት ጋር ተያይዞ የሚመጡ አደጋዎች። (ከወገብ በታችም ይሁን ሙሉ ማደንዘዣ)
ከኦፕሬሽን በውሀላ
- ኢንፌክሽን መኖር (የማህፀን ኢንፌክሽን፣ የቁስሉ መመርቀዝ እና መግል ማውጣት)
- የደም መርጋት
- ሆስፒታል ለተወሰነ ቀን መቆየት
- ኦፕሬሽን አንድ ጊዜ ከተደረገ በውሀላ ለቀጣይ የእንግዴ ልጅ ከፅንሱ ቀድሞ መምጣት፣ የእንግዴ ልጅ ኦፕሬሽን በተደረገበት ላይ መጣበቅ እና ወደ ማህፀን ግድግዳ ላይ ማደግ ይህም የሚቀጥለው ወሊድ ከባድ እና ደም መፍሰስ እንዲኖር እና እስከ ማህፀን መውጣት ማድረስ
- ቀጣይ እርግዝና ላይ ማህፀንና የሆዳችን ሽፋ መጣበቅ እና የአሁኑን ኦፕሬሽን ከባድ ማድረግ …
በኦፕሬሽን በድጋሚ ልወልድ የምችለው ወይም የምገደደው ምን ነገር ከገጠመኝ ነው?
- ከአንድ በላይ በኦፕሬሽን ወልደሽ ከሆነ
- ፅንሱ ከ4 ኪ.ግ በላይ ከሆነ
- በፊት የተደረገልሽ ኦፕሬሽን ምክንያት የአሁኑ ሊሰራልሽ የተባለበት ምክንያት ከሆነ
- በፊት የተሰራልሽ በተረጋገጠ የማህፀን ጥበት ምክንያት ከሆነ
- ከዚህ በፊት በነበረሽ እርግዝና በምጥ ጊዜ የማህፀን መተርተር የገጠመሽ ከነበረ
- ሀኪምሽ በኦፕሬሽን መውለድ ያለውን ተጓዳኝ ጉዳት ከነገረሽ እና ከተረዳሽ በውሀላ ….አይ ቢሆንም በኦፕሬሽን ነው ምፈልገው የምትይ ከሆነ
- በፊት የተሰራልሽ ኦፕሬሽን classical cs ወይንም ልጁ የወጣው በላይኛውና በፊተኛው የማህፀን ግድግዳ ሆኖ በቋሚ ቅድ አይነት ሲሆን
- በፊት myoma ለተባለ የማህፀን እጢ(እባጭ) ኦፕሬሽን ከተሰራልሽ ፤ ይህም እጢው የማህፀንሽን ሙሉ ግድግዳ ይዞ የነበረ ከነበረ እናም ሀኪም ወደፊት በኦፕሬሽን ነው የምትወልጂው የሚል የተፃፈ ወረቀት ወይም በቃል ከተነገረሽ።
በማህፀን አምጦ የመውለድ ጥቅሞች ከኦፕሬሽን አንፃር
- በማህፀን መውለድ ኢንፌክሽን የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል
- ለከፋ የደም መፍሰስ እድልን ይቀንሳል (ከcs አንፃር)
- የእናቲቱን ሆስፒታል ለህክምና የመቆየት ጊዜዋ ይቀንስላታል።
- እናቲቱ በወለደች ጊዜ በ30 ደቂቃ ውስጥ ያለምንም ችግር ልጇን ማጥባት መቻል
- ለተለያዩ የማደንዘዣ መድሀኒቶች የመጋለጥ እድልን መቀነስ እና ከወሊድ በውሀላ ሊመጣ የሚችል የማደንዘዣ መድሀኒት የጎንዮሽ ችግር አለመኖር
- በቀጣይ እርግዝና ላይ አሉታዊ ተፅዓኖ አለመኖር…
ዶ/ር ዳዊት መስፍን፤ የማህፀንና ፅንስ ስኜሻሊስት 0911138054
Join the following telegram and Facebook channel for more
https://t.me/DrDawitMOBGYN
https://www.facebook.com/DrDave.OBGYN/