በሲዳማ ክልል አለታ ወንዶ ከተማ ወስጥ የሚገኝ ተቋም ነው። ተቋሙ እስከ 2009 ዓ.ም ድረስ ጤና ጣቢያ (Health Center) ነበር። 2009 መጨረሻ አከባቢ ወጣቱ መሪ አቶ ፍፁም ዳንጉራ የሚባል በቀድሞው ደቡብ ብሔር ብሔረሰብ ክልልና በሲዳማ ዞን አማካኝነት የጤና ጣቢያ ሀላፊ አድርጎ ሹመት ተሰጠው።
ወጣት መሪ አቶ ፍፁም ዳንጉራ ብዙም ሳይቆይ የዞኑ ካቢኔ ጋር በመነጋገር ከጤና ጣቢያ ወደ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እንድያድግ ታስቦ የተሰራውን ህንፃ በማስመረቅ ከክልሉ ጤናና ጤና ነክ ዳይሬክቶሬት በመጋበዝ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እንዲሆን የሚጠበቅበትን አሟልቶ በ2010 ዓ.ም የአለታ ወንዶ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሆኖ በይፋ ስራውን አስጀመሩ።
አቶ ፍፁም ዳንጉራ በስራቸው ድርድር የማያውቁ በስራ የሚያምኑ፣ በሳል ፣ ሰውን የሚወዱ ፣ ከአቻ ተቋማት ጋር ድፕሎማሲ በመፍጠር በትብብር መስራት ጥበብ የተካኑ ወጣት መሪ ናቸው። ይህ ብቻ አይደለም ተቋሙ በክልል ውስጥ ካሉ ከመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ወስጥ ግንባር ቀደምና ተሸላሚ ተቋም ነበር።
ሲዳማ ክልል ሆኖ ከተደራጀ በኃላ የአለታ ወንዶ ከተማና የአከባቢው ማህበረሰብ አሁንም ሆስፒታል አንድ ደረጃ ከፍ ማለት አለበት የሚል ፍላጎት እየጨመረ መጣ። ትዝ ይለኛል በ2014 ዓ.ም የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የ2014 ዓ.ም በጀት አመት የአፈፃፀም ግምገማ ና የ2015 በጀትና እቅድ ስብሰባ ላይ የተከበሩ አንድ የምክር ቤት አባል የአለታ ና የአከባቢው ማህበረሰብ የአለታ ወንዶ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ወደ አጠቃላይ ሆስፒታል እንዲያድግ ይፈልጋል ብሎ አንስቶ፣ በሰዓቱ ክቡር የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ መልስ የነበረው የማህበረሰብ ጥያቄ ተገቢ መሆኑን በማንሳት የግዜ ጉዳይ ነው በቅርቡ እናሳካለን ብሎ ነበሩ።
በ2015 ጀምሮ የማህበረሰብ ጥያቄ እየጨመረ ሲሄድ የሆስፒታሉ መሪ አቶ ፍፁም ዳንጉራ ከማናጅመንታቸው ጋር በመነጋገር የግድ ሆስፒታሉ ወደ አጠቃላይ ሆስፒታል ማደግ አለበት ብለው አስወሰኑ። ይህ ብቻ አይደለም ከከተማ አስተዳደር፣ ከዞን አስተዳደር እንዲሁም ከክልል አስተዳደር ጋር በመሆን ተቋሙ ማሟላት የሚጠበቅበትን ነገር ሁሉ አቅም በሚፈቅደው መልኩ እየሰራ ቆይቷል።
ካለው Resource አንፃር ብዙ Challenge ቢገጥመውም አጋጣሚዎችን ሁሉ በመጠቀም ሆስፒታሉን በተለይም በMedical Equipment ማደራጀትን ቀጠለበት። ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመናበብ በክልል ጤና ና ጤና ነክ ባለስልጣን መጥቶ ሆስፒታሉን ማየት እንዳለባቸው ከተስማሙ በኃላ የግዜ ቀጠሮው ተያዘ።
በተሰጠው የግዜ ገደብ በመጠቀም አጠቃላይ ሆስፒታል ለመሆን ማሟላት የሚጠበቅበትን ነገር እንድያሟላ አቶ ፍፁም ዳንጉራ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቆራጥነት ስራቸውን ቀጠሉ። ይህ ብቻ አይደለም ከዞኑ አስተዳዳሪ ክቡር አቶ መንገሻ ፊታሞ ና ከከተማ ከንቲባ ዶ/ር ባራሳ ባልጉዳ ጋር በመሆን ማህበረሰብ በማንቃት ሃብት የማሰባሰብ ስራ አስጀምሩ።
አቶ ፍፁም የሆስፒታሉን ባለሙያዎች ሳይቀር አቅማቸው የፈቀደውን ለዚህ ለተቀደሰ ሀሳብ በበጎ ፈቃዳቸው አንዲደግፉ ሀሳብ ካቀረቡ በኃላ ሁሉም ባለሙያ ማለት በሚቻል ደረጃ የአቅማቸውን ለገሱ።
ይህ ብቻ ሳይሆን የከተማ የዞን እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሳይቀር ገንዘብ በማጣት ሆስፒታል በተለይ በሕክምና መሳሪያ ለአጠቃላይ ሆስፒታል የሚመጥን ቁመና እንዲይዝ ተደርጓል። አቶ ፍፁም የትኛውም የሚገጥማቸውን Challenge ወደ መልካም ዕድል የመቀየር እምቅ አቅም የተቸራቸው ታታሪ መሪ ናቸው ።በ2016 በጀት አመት የአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል በዞኑ በከተማ እንዲሁም በክልል ካሉ ተቋማት ተመዝኖ በግምባር ቀደምትነት አጠናቀው ባለ ሶስት ዋንጫ ተሸላሚ ሆኖአል።
ፍፄ የሲዳማ ህዘብ ያመሰግንሃል በርታልን….!
From Aleta Wondo General Hospital staff,
Buye kada: Biomedical Engineer
Yohannis Habtegiorgis: Quality Officer
@HakimEthio