በእርግዝና ጊዜ ስለሚከሰተው ማቅለሽለሽና ማስታወክ ምን ያህል ያውቃሉ?
– በዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት
⁃ ማቅለሽለሽና ማስታወክ ሁሉም እርጉዝ እናቶች እስከ 4 ወራቸው ድረስ የሚያጋጥማቸው የህመም አይነት ነው፡፡
⁃ አንዳንዶች ምንም ሳይኖራቸው አንዳንዶች ደግሞ ከ4 ወር በላይ ቆይቶ ሊያስቸግራቸው ይችላል
⁃ አንዳንድ እናቶች ላይ ጠንከር ብሎ የእለት ተእለት ስራቸውን እንዳያከናውኑና ሲብስ ደግሞ ሆስፒታል ገብተው መታከም እስኪኖርባቸው ድረስ ሊሆን ይችላል።
ማድረግ ያለብሽ ጥንቃቄዎች
⁃ ጠዎት ካልጋሽ ሳትነሺ ትንሽ ምግብ ተመገቢ
⁃ ምግብሽን ቁርስ ፣ ምሳ እና እራት ብለሽ ሳትከፉፍይ… በየ2-3 ሰዓት ልዩነት ትንሽ ተመገቢ (ሆድሽ ባዶ መሆን ወይም መጥገብ የለበትም)
⁃ ምግብሽን በችኮላ አትመገቢ። ተረጋግተሽ ጊዜ ወስደሽ ተመገቢ
⁃ ከተመገብሽ በውሀላ ንፁህ አየር ወዳለበት መሆንን አትርሺ
⁃ የመመገቢያ እና የመኖሪያ ቦታን ለዪ (ሽታ ሊያባብስብሽ ስለሚችል)
⁃ ትንሽ ትንሽ ፈሳሽ በየምግብ መሀሉ ውሰጂ
⁃ ቤትሽ በተቻለ መጠን ንፁህ እና ፍፁም ከሽታ ነፃ መሆኑን አትዘንጊ
⁃ ዶድራንት ፣ ሽቶ፣ እና ሽታ ያላቸውን ቅባቶች አስወግጂ
⁃ ቤትሽ ውስጥ ጫጫታን በተቻለ መጠን አስወግጂ
⁃ ባልሽ እና ቤተሰቦችሽ ከሌላው ጊዜ በተለየ ላንቺ ጤንነት ከፍተኛ አስተዋፅዎ ስለሚኖራቸው አቅርቦታቸውን ጨምሪ
አመጋገብሽ መሆን ያለበት
– በመጠኑ ትንሽ ምግብ
– ቀዝቀዝ ያለ
– ደረቅ ያለ እንደ ጥራጥሬ ፣ ደረቅ ዳቦ እና ኩኪስ የመሳሰሉ
– ብዙም ቅመም ያልበዛበት ፣
– የተጠበሰ እና ቅባት የበዛበት ምግብ አይመከርም
– ብዙም ጣፉጭ ያልሆነ
– ኮምጠጥ ያለ እና የሎሚ ጣዕም ያለው መጠጥ ማዘውተር
– የዝንጅብል ሻይ መጠጣት
– የዝንጅብል ቃና ያላቸው ከረሜላዎችን መጠቀም
– አልኮል ፣ ቡና እና ጠቆር ያለ ሻይ በፍፁም አይመከርም
ይህ ሁሉ አድርገሽ ካልተሻለሽ እና ኪሎ ከመጠን በላይ ከቀነስሽ ጊዜ ሳትሰጪ ሀኪምሽን አማክሪ።
ዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ስልክ: 0911138054
Join the following telegram channel for more https://t.me/DrDawitMOBGYN
@HakimEthio