በኢትዮጵያ ውስጥ ነርስ ስትሆን ብዙ ስሞችን ታገኛለህ መርፌ ወጊ፣ አልጋ አንጣፊ ፣ ቁስል አጣቢዎቹ ወዘተ…. ትባላለህ።

አብዛኛዉ ታካሚ የሀኪሞች ፀሀፊ አድርገው ነው የሚያስቡን። ለሁሉም ሰው punching bag ትሆናለህ። በምትሰራበት ቦታ ሁሉንም ነገር ትሆናለህ ሀኪም ፣ ጥበቃ ፣ ፅዳት ሰራተኛ ፣ አስተዳደር አንዳንዴም ታካሚ ትሆናለህ።

አብዛኛውን ጊዜ ሞያችን ምን እንደሆነ እንኳን የማንረዳበት ሁኔታ ውስጥ እንገባለን። ምን አለፋችሁ አንድን ስራ የሚሰራው ሰው ካልተገኘ ነርሶቹ ይሰሩታል ይባላል።

በሆስፒታል ውስጥ የማንሆነው ነገር የለም የውሀ ቧንቧ እንጠግናለን፣ የተበላሸ በር አናስተካክላለን፣ Receptionist ነን ነርሶች የማያውቁት ነገር የለም እንባላለን። ከሞያችን በተጨማሪ ሁሉንም ነገር ሆነን እንሰራለን።

Professional መሆናችን እራሱ ይረሳል። ነርስነት ላንቺ ምንድን ነው ብትሉኝ ሁሉንም ነገር መሆን ነው። ነገር ግን ሁሉንም ነገር ሆነን ሳለን በቂ ክፍያ እንኳን የለንም። We are over worked but under paid.

እኔም ሆንኩ ባካባቢዬ ያሉ ነርሶች ሁሌም እንዴት ከዚ ስራ እንደምንወጣ ነው ሁሌም የተሻለ ነገር እንፈልጋለን። ሳንፈልግ ሞያውን እንድንጠላው እየሆንን ነው።

We are under paid, over worked, we lack respect from our coworkers, our managements and patients. We can’t even pay our rent.

ሁሌም ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት ሌሎች አማራጮችን እንደፈለግን ነው። ተምረን እንኳን የተሻለ እድገት ወይም ደሞዝ የለንም። Social life የለንም፣ በአላትን አናከብርም፣ ከቤተሰብ ጋር በቂ ጊዜ የለንም፣ ሰርግ እና ሀዘን ላይ አንገኝም።

In my opinion በቂ እረፍት የሌለው፣ በስራ ቦታው ሁኔታ ደስተኛ ያልሆነ፣ በቂ ክፍያ የማያገኝ ሰራተኛ productive ሆኖ ስራውን መስራት አይችልም። Overall ጤና ዘርፍ ውስጥ ያለን ሰዎች we need change!!!

Sr Gelila K.

YouTube: http://www.youtube.com/@Hakim207?sub_confirmation=1

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *