የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 31ኛ ዙር የህክምና ምሩቃን የነበሩ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎችና ከሀገር ውጭ በህክምናው ዘርፍ ሙያዊ ግዴታቸውን በመወጣት ላይ የሚገኙ ሲሆን የ10ኛ ዓመት የምረቃ በአላቸውን ለማክበር በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡
አነዚህ ተመራቂዎች በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ በነበሩበት ወቅት በሚያደርጉት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና በነበረው ጠንካራ የተማሪዎች ህብረት በስኬታማ ስራዎች ይታወቁ ነበር፡፡ እነዚህ ሀኪሞች በህክምናው መስክ በተናጠል እያደረጉ ያሉት አስተዋፅኦ ይበልጥ ፍሬያማ እንዲሆን እና ለመደጋገፍ እንዲያመች ጥቅምት 9/ 2017 ዓ.ም ሁሉም ከያሉበት በመሰባሰብ ምክክር ለማድረግ አስበዋል።
ስለሆነም ህብረቱ ዩኒቨርሲቲውን ለማገዝ እንዲሁም የጤና ዘርፉን ለመደገፍ ላሰበው በጎ ተግባር በኢትዮጲያ ውስጥና ከኢትዮጵያ ዉጭ ያላችሁ ሃኪሞች ሸራተን አዲስ በመገኘት በመርሀግብሩ ተሳታፊ እንድትሆኑ ሲል “የጎልደን ባች ሪዩኒየን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ” ጥሪውን ያስተላልፋል።
ለልህቀት እንተጋለን!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
16/01/2017 ዓ/ም
Join the University of Gondar’s 31st medical graduates as we celebrate our 10th anniversary reunion. Let’s come together to reconnect, mark this special occasion, and form an alumni association dedicated to supporting UOG, CHS Hospital, and advancing healthcare.
Celebrating the 10th year anniversary of Medical Graduates of UOG’s 60th Diamond Jubilee.
Date: October 19th
Venue: Sheraton Addis
Golden Batch Reunion Executive Committee
University of Gondar