የቁስል ህክምና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ራሱን የቻለ ህክምና ነው፡፡ ከነርሶች አንስቶ እስከ ሀኪሞች ድረስ የዚህን ህክምና ልዩ ስልጠና (Speciality)  እየወሰዱ የቁስል ህክምናን ያደርጋሉ፡፡ የቁስል ህክምና እንደ ሰርጀሪ ፤ የአጥንት ህክምና እና የፕላስቲክ ሰርጀሪ ካሉት ልዩ ህክምናዎች ጋር በቅርበት ቢዛመድም ከነዚህ ህክምናዎች ጋር አንድ አይነት አይደለም፡፡

የቁስል ህክምናን ምን ልዩ ያደርገዋል?

የተለያዩ ቁስሎች የተለያየ ህክምና ነው የሚያስፈልጋቸው፡፡ በሀገራችን ሁሉም ቁስሎች በአንድ አይነት መንገድ ሲታከሙ ይስተዋላል፡፡ የቁስል ህክምና እያንዳንዱን ቁስል እንደአይነቱ ለይቶ ያክማል፡፡

ሁሉም ቁስሎች በአንድ አይነት ግብዓት (ማቴሪያል) ነው የሚታከሙት?

አይደለም! ቁስሎች እንደ አይነታቸው በተለያዩ ግብዓቶች ነው የሚታከሙት፡፡ ለቁስሎች በቶሎ ወይም በጭራሽ አለመዳን እንደምክንያት የሚጠቀሰው ለዛ ቁስል ተገቢውን ግብዓት አለመጠቀም ነው፡፡

ዶ/ር ፌቨን ሞገስ
ጠቅላላ ሀኪም ፤ የስቶማ እና ቁስል ህክምና አማካሪ

በዶ/ር ፌቨን ለመታከም ከፈለጉ በ 09-73-40-23-86 ደውለው ቀጠሮ ይያዙ፡፡

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *