በልጅነቱ አባቱ ቦሩሜዳ ሆስፒታል እየወሰዱ “አንድ ቀን አንተም እንደነዚህ ሀኪሞች የቀዶ ጥገና ዶክተር ትሆናለህ” እያሉት ነው ያደገው። ጅማ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ህክምና ጀመረ። ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ከተመረቀ በኋላ ጥቂት ሰርቶ በቀዶ ጥገና ስፔሻላይዝ አደረገ።

ዶ/ር ኑሩ ለብዙ ሰዎች የተለያዩ ቀዶ ጥገናዎች ሰርቷል። የጭንቅላትና የህብረሰረሰር ቀዶ ጥገና ሰርቶ ብዙዎችን አክሟል። ብዙ ታካሚዎች ICU ገብተው ፅኑ ህክምና እንዲያገኙ አድርጎ ያውቃል።

አንድ ቀን ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር እየሄደ በተፈጠረ የመኪና አደጋ በቅፅበት ሀኪሙ ወደ ታካሚነት ተለወጠ። የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ሲሰራ የነበረው ሀኪም የጭንቅላት ቀዶ ጥገና የሚያስፈልገው ታካሚ ሆነ። በደረሰበት ጉዳት መናገር አቅቶት የፅኑ ህክምና ክፍል ICU ገባ።

ዶ/ር ኑሩ ሞት አፋፍ ደርሶ ተመሷል። የህመሙን ጉዞ፣ ICU ውስጥ ያሳለፋቸውን ከባድ ጊዜያት፣ የፅኑ ህክምና ክፍል ውስጥ ስለሚከሰተው ቅዠት (ICU psychosis)፣ ወደ ህክምና ለለመለስ ሲያስብ የገጠመውን ፈተና፣ ስለህይወት ያለውን እይታ፣ ስለ ተአምራዊ ፈውስ ያለውን ምልከታ በዚህ ቪዲዮ በዝርዝር አቅርቧል።

ዶ/ር ኑሩ ስለሀይማኖት፣ ስለተስፋ፣ ስለ ፅናት፣ ስለቤተሰብ ፍቅር፣ ስለ እምነት፣ ስለ ታካሚን ማእከል ያደረገ ህክምና (Client-centered care)፣ ስለሀኪምነት ብዙ እንድናስብ የሚያደርጉ፣ ስራችንን ላይ መልካም ተፅእኖ የሚያሳድሩ ሀሳቦችን አንስቷል።

ዶ/ር ኑሩ ስለጥንካሬህ፣ ስለፅናትህ እና ስላካፈልከን ሀሳቦች አመሰግናለሁ። ብዙ የተማርኩበት ቪዲዮ!!!!!! ሁላችሁም በተለይ የጤና ባለሞያዎች እንድታዩት እጋብዛለሁ።

ዩዴሞኒያ ለሁላችን!!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው ፤ የአእምሮ ህክምና ሀኪም

Follow Hakim via

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *