1. የአእምሮ ሕመም የድክመት ወይም የግል ውድቀት ምልክት ነው።
እውነታው:- የአእምሮ ሕመም በግል ድክመት ወይም በፍላጎት እጥረት ያልተከሰቱ እና እንደ ሌሎች አካላችን(Organ) በተለያዩ ምክንያት ሊታመም የሚችል አካላችን ነው።
2. የአእምሮ ሕመም ያለባቸው ሰዎች አደገኛ ወይም ጠበኛ ናቸው።
እውነታው:- አብዛኛዎቹ የአእምሮ ህመምተኞች አደገኛ አይደሉም እና ከማንም በላይ ለጥቃት የተጋለጡ ናቸው።
3. የአእምሮ ህመም እድሜ ልክ የማይድን ህመም ነው።
እውነታው:- ብዙ የአእምሮ ሕመሞች ሊታከሙ የሚችሉ ናቸው፣ እናም አእምሮ ህሙማን በጊዜ ሕክምና ካገኙ የተሻለ ህይወት መኖር ይችላሉ።
4. የአእምሮ ሕመም የሚያጠቃው የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ ነው።
እውነታው:- የአዕምሮ ህመም እድሜ፣ ጾታ፣ ዘር፣ ጎሳ ወይም ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ሳይለይ ማንንም ሊጎዳ ይችላል።
5. መድሃኒት ለአእምሮ ህመም ብቸኛው ህክምና ነው።
እውነታው:- መድሀኒት የህክምናው አስፈላጊ አካል ቢሆንም፣ የንግግር ሕክምና፣ የምክር እና የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች በጣም ውጤታማ የህክምና አማራጭ ሊሆኑ ይችላሉ።
6. የአእምሮ ሕመም ተላላፊ ነው።
እውነታው:- የአእምሮ ህመም እንደ አካላዊ ሕመም ከሰው ወደ ሰው ተላላፊ አይደለም። የአእምሮ ህመም በስነፍጥረታዊ፣ ስነልቦናዊ እና ማህበራዊ ምክንያት የሚከስት ህመም ነው።
7. የአእምሮ ሕመም የሚያጠቃው አዋቂዎችን ብቻ ነው።
እውነታው:- ልጆች እና ጎረምሶች እንደ ድብርት፣ ጭንቀት፣ ADHD እና ሌሎች ያሉ የአእምሮ ጤና ሁኔታዎችን ሊጠቁ ይችላሉ።
8. ለአእምሮ ጤንነት እርዳታ መፈለግ የግል ድክመት ምልክት ነው።
እውነታው:- በእርግጥ እርዳታ እና ህክምና መፈለግ የጥንካሬ ምልክት ነው።
NB: በእነዚህ አፈ ታሪኮች ምክንያት ብዝዎች ሕክምና እንዳያገኙ፤ እርዳታ እንዳይፈልጉ ተደርገዋል። እንዲ እባላለሁ በማለት ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ብዙዎች ቤት ወስጥ ታስረዋል፤ ውጪ ማየት ትተዋል። ቆም ብለን እናስብ ሰዎች እራሳቸው አጠፉ የሚለው ዜና መስማት ተበራክቱዋል እኛ ቀርበን ከማውራት ከመረዳት ይልቅ እነዚህን አፍ ታሪኮችን ማለት ይቀለናል 🤔።
ዛሬ ይህ መልዕክት ለእናንተ ነው። ማገዝ ባንችል እንዲታገዙ እናድርግ እንዚህን አፍ ታሪኮችን በማዎቅ እና በማስተካከል መገለልን ለመቀነስ፣ ግንዛቤን ለማስፋት እና ሰዎች ለአእምሮ ጤና ጉዳዮች የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ እና እንክብካቤ እንዲያገኙ እናድርጋቸው።
የእናንተን ሃሳባ አካፍሉን🙏 አመሰግናለሁ
ነብዩ ጃግሶ (ስነ አእምሮ ባለሙያ)
Source: https://aneweratms.com/10-common-myths-about-mental-illness/ and from my personal experience.
ቴሌግራም https://t.me/psychiatry1
@HakimEthio