በቅድሚያ እንደ ሁልጊዜውም ለሀኪሙ እና ለአጠቃላይ ጤና ባለሙያው ድምፅ እየሆናችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።

ከታች በምስሉ እንደምትመለከቱት ከሶስት ሳምንታት በፊት በሲዳማ ክልል የወንዶ ገነት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በዜሮ አመት የስራ ልምድ ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት እጩ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ ለመቅጠር ገለልተኛ የተባሉ አካላት በተገኙበት ከሞላ ጎደል ፍትሐዊ የሚባል እና ሁለት ሙሉ ተከታታይ ቀናትን የ ፈጀ የፅሁፍ እና የ ቃል ፈተና ፈትኖን ማለፋችን እና የ ቅጥር ቀኑን እንድንጠብቅ ተነግሮን በመጠበቅ ላይ እያለን ከእኛ እውቅና ሙሉ ለሙሉ ውጪ በሆነ ምክንያት ስማችንን ከቅጥሩ ስም ዝርዝር ውጪ በማድረግ ለጥፈዋል።

ለዚህም ማብራሪያ እንዲሰጡን በጠየቅን ጊዜ ነገሩ ከነሱ አቅም በላይ መሆኑን እና ከክልል በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ማስታወቂያው ላይ የስራ ልምድ ዜሮ አመት የሚለው ሲተረጎም የትም ቦታ ሰርቶ የማያውቅ ማለት እንደሆነና የእኛ ስም ክልሉ ውስጥ ከሚገኙ ሆስፒታሎች ጋር ተያይዞ እንደሚገኝ ማረጋገጥ በመቻላቸው እንደሆነ ገልፀውልናል።

እኛም የተሻለ ምላሽ ብናገኝ ብለን ወደ ክልሉ ጤና ቢሮ እና ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ቀርበን ስንጠይቅ የሰጡን ምላሽ ተመሳሳይ እና በኛ እይታ አጥጋቢ ሆኖ አላገኘነውም

ለሐኪም ቤተሰቦች ጉዳዩን ግልፅ ለማድረግ ያህል ጥያቄያችን

1ኛ. ዜሮ አመት የስራ ልምድ ተብሎ ማስታወቂያ ሲወጣ ምን ማለት ነው? እኛ እንደተረዳነው “The Minimum required experience” ነው ወይስ እነሱ እንደሚሉን “Exclusively or the maximum required experience” ነው?
የፐብሊክ ሰርቪስ ህጉስ ይሄን በተመለከተ ምን ይላል?

2ኛ. እንደዚህ አይነት የተለየ አሰራር ስለመኖሩ ለመናገር መሞከራቸው ፈተናውን ከጨረስን በኋላ እና የቅጥር ጊዜያችንን በመጠባበቅ ላይ ባለንበት ጊዜ ላይ መሆኑስ የተወሰኑ ሰዎችን በ Favoritism ለመጥቀም ታስቦ አይደለም?

3ኛ. ከመካከላችን ላለፉት ሁለት ወራት እና ከዚያ በላይ በግል ምክንያት በፊት ከሚሰሩበት አቋርጠው ቤታቸው ተቀምጠው ያሉ ሐኪሞችን አሁንም ድረስ እየሰሩ እንደሚገኙ አድርጎ ማቅረብና ይኼንንም ላለመቅጠር እንደምክንያት አድርጎ መጠቀሙስ አግባብ ነው?

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *