አንጎል በውሐ የተከበበና የተከፋፈለ ነው ። ውሐ መሳይ የአንጎል ፈሳሽ በቦይ ውስጥ እየተዘዋወረ ለአንጎል ምግብ የማድረስ ፣ተረፈ ምርቶችን የማስወገድ አገልግሎት ይሰጣል ። ከውጪም ሆነ ከውስጥ የሚሰነዘሩ የአንጎል ጥቃቶችን ያመክናል ። አንጎል የውሐ ሻወር እንዲያገኝ የሚስችል ተፈጥሯዊ መዋኛ ቦይ-ስረዓት ያለው ድነቅ ባለ ደሴት የድንቅ ፍጡር አካል ነው ።
ውሐ መሳይ የአንጎል ፈሳሽ መዘዋወሪያ ቦይ በልዩ ልዩ ምክነያቶች ሲለጠጥ የአንጎል ቦይ መለጠጥ /Hydrocephalus / ይባላል ። ችገሩ በየትኛውም የእድሜ ክልልና ፆታ የሚከሰት ቢሆንም መነሻ መንስኤዎቹ ግን በእድሜ ክልል የተለያዩ ናቸው ።
በህፃናት ላይ እንደዚህ አይነት የአንጎል ህመም ሲከሰት የራስ -ቅላቸው ከመጠን በላይ ይለጠጥና ትልቅ ጭንቅላት እንዲኖራቸው ያደርጋል ። የራስ ቅሉ መለጠጥ የመጣው የአንጎል ቦይ በመለጠጡ ነው ።ህፃናትን ለዚህ የአንጎል ህመም ከሚዳርጉ ተጠቃሽ ምክነያቶች ጥቂቶ የሚከተሉት ናቸው ።
የጨቅላ ህፃናት እስትሮክ ። እስትሮክ ሲባል የአዛውንት ህመም ነው የሚል እሳቤ አለ ።ነገር ግን እስትሮክ በእድሜ የማይገደብ አደገኛ ድንገተኛ የአንጎል አካላዊ ህመም ነው ። በተለይ ያለ ግዜአቸው የተወለዱ አለያም የውልደት ክብደታቸው ዝቅተኛ ሆነው የተወለዱ ህፃናት ለአንጎል ቦይ መድማት ችግር ይጋለጣሉ ። ደም ወደ አንጎል ቦይ በመፍሰሱ ምክነያት ተፈጥሯዊ የአንጎል ፈሳሽ ዝውውርን ያስተጓጉላል ። በዚህ የተነሳ ፈሳሱ በቦዩ ውስጥ በመጠራቀም በግዜ ሒደት ቦዩን ይለጥጠዋል ። በቂ የእርግዝና ክትትል በማድረግ እንደዚህ አይነት ችግር እንዳይፈጠር ይረዳል ።
በእርግዝና ወቅት አለያም ከተወለዱ በሗላ በሚከሰት የአንጎል ውስጥ ኢንፌክሺን አማክኝነት ችግሩ ሊፈጠር ይችላል ። በተለይ ከእናት ወደ ፅንስ የሚዛመቱ ተላላፊ ኢንፌክሺኖች ለዚህ ችግር ይዳርጋሉ ። በህፃንነት ወቀት የሚከሰት የማጅራት ገትር የአንጎል ሽፋን ብግነትም ሌላኛው መንስኤ ነው ። በነዚህና መሰል የጤና እክሎች የሚከሰት የአንጎል ቦይ መለጠጥን በቅደመ መከላከል መርህ ማስቀረት ይቻላል ። ክትባት በማስከተብ እንከላከለዋለን ።
የአንጎል እጢ ልላኛው መንስኤ ነው ። በተለይ በውስጠኛውና በሗለኛው የአንጎል ክፍል የሚነሱ እባጮች የዚህ ችግር ተጠቃሽ መንስኤዎች ሲሆኑ ይታያል ።እንዲሁም በእርግዝና ወቅት በሚፈጠር የቫይታሚን እጥረት ሳቢያ በፅንሱ አንጎል አፈጣጠር ላይ ችግር ፈጥሮ ለተመሳሳይ የአንግል ችግር ይዳርጋል ። folic acid ከእርግዝና ቀደም ብለው አለያም እርግዝና እንደተፈጠረ በመውሰድ ከዚህና ከሌላ የአንጎልና ህብረሰ ሰረሰር አፈጣጠር ችግር ይጠብቁ ። ያ’ው በኛ ሀገር እርግዝና የሚታወቀው መቼ እንደሆነ ስለሚታወቅ የማርገዝ ሐሳብ ሲኖር ቀድሞ መውሰዱ የተሻለው ምክር ነው ።በዘረ መል ችግር እና በአካላዊ የአንጎል ምት ምክነያት የሚመጣም አለ ።
የአንጎል ቦይ መለጠጥ በአፋጣኝ ካልታከመ በአዳጊ አንጎል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል ።ቀስ እያለም ተጎቺዎችን ለልዩ ልዩ ተጨማሪ የአንጎል ህመሞች አጋልጦ ይሰጣል ።የሰውነት መስነፍ፣የመስማትና ማየት አክል እስከ አንጎል እድገት ውስንነት ያደርሳል ። ችግሩን በቅንጅት እና በትብብር መከላከል ህክምና እንዲያገኙ የህክምና አማራጮችን ማስፋት ተገቢ ነው ።
መከላከል ቀዳሚ እና ወደር የማይገኝለት የህክምና ዘዴ ነው ። ህክምና ሲባል መርፌ አለያም ቀዶ ህክምና ማድረግ አይደለም ። ይኸ የመጨረሻው የህክምና አማራጭ ነው ። የመጀመሪያው የዘመናዊ ህክምና አማራጭ ቅድመ -መከላከል ዘዴ ነው ። ቅድመ እርግዝና ምርመራ በማድረግ በተለይ የአባላዘር ችግር ካለ መታከም።በእርግዝና ወቀትም ተገቢውን ክትትል በማድረግ ከዚህ ህመም መጪውን ልጆን ይጠብቁ ። የሚታከሙ ህመሞችን በማከም ለማከም ውስብስብስብ የሆኑ ህመሞችን እናክም ።
ከመከላከል መርሆ አለያም ከአቅም በላይ በሆነ ምክነያት የሚፈጠር የአንጎል ቦይ መለጠጥን በመድሐኒትና በቀዶ ህክምና ማከም ይቻላል ። ልጅዎ የራስ ቅሉ ከመላ ሰውነቱ አንፃር ገዝፎና ተልቆ ካዩ ወደ ህክምና ቦታ ውስደው የራስ ቅሉ ትክክለኛነት ያረጋግጡ ። የራስ ቅል ልኬት ማድረግ ቀላል የመለያ መንገድ ነው ። በተለይ ለክትባት ሲሔዱ የልጁን የራስ ቅል ልኬት ይወቁ ።
References
Jankovic J, Mazziotta JC, Pomeroy SL, Newman NJ, Bradley WG (Walter G. Bradley and Daroff’s neurology in clinical practice, eight’s edition P 1854-57

ዶ/ር መስፍን በኃይሉ ፤ ጥቁር አንበሳ
Youtube: http://www.youtube.com/@Hakim207?sub_confirmation=1
@HakimEthio