የፈለገ ሕይዎት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ እና የዐይን ቆብ ፀጉር መቀልበስ ቀዶ ሕክምና እንደሚሰጥ አስታውቋል።
በፈለገ ሕይዎት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዐይን ሕክምና ክፍል አሥተባባሪ ኦፕቶሜትሪስት ተስፋዓለም ጋሻው እንዳሉት ከኅዳር 8-12/ 2017 ዓ.ም በፈለገ ሕይዎት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ እና የዐይን ቆብ ፀጉር መቀልበስ ቀዶ ሕክምና ይሰጣል።
ሕክምናው “ኪዩር ብላይንድነስ ፕሮጀክት” ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር እንደሚሰጥ ነው የገለጹት።
የዐይን ሞራ ግርዶሽ እና የዐይን ቆብ ፀጉር መቀልበስ ቅድመ ልየታ እና ምርመራ ሥራ በሚከተሉት ቦታዎች የሚሰጥ ይኾናል።
1ኛ. ከጥቅምት 16-17/ 2017 ዓ.ም በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በጓንጓ ወረዳ እና ቻግኒ ከተማ ቻግኒ ጤና ጣቢያ፣ በባንጃ ወረዳ እና እንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ለሚገኙ በእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል፣
2ኛ. ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም በሰሜን ጎጃም ዞን ሰሜን አቸፈር ወረዳ ሊበን ሆስፒታል፣
3ኛ. ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም በሰሜን ጎጃም ዞን ሰሜን አቸፈር ወረዳ ይስማላ ጊዮርጊስ ጤና ጣቢያ፣
4ኛ. ከጥቅምት 19-21/ 2017 ዓ.ም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሁለት እጁነሴ ወረዳ ደብረ ጉባዔ ጤና ጣቢያ፣
5ኛ. ከጥቅምት 23-24/2017 ዓ.ም
➽. በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዳንግላ ወረዳ ዳንግላ ጤና ጣቢያ፣
➽. በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ ቁሃር ጤና ጣቢያ
➽. በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሁለት እጁነሴ ወረዳ ሞጣ ሆስፒታል
6ኛ. ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም
➽. በደቡብ ጎንደር ዞን ወረታ ከተማ እና አካባቢው የሚገኙ በወረታ ጤና ጣቢያ፣
➽. ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ ዱርቤቴ ሆስፒታል፣
7ኛ. ከጥቅምት 23-30/ 2017 ዓ.ም ባሕር ዳር እና አካባቢው በፈለገ ሕይዎት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣
ሌሎች ከተጠቀሱት ቦታ ውጭ የኾኑ እና አገልግሎቱን ማግኘት የሚፈልጉ ደግሞ በሚቀርባቸው በተጠቀሱት ቦታዎች እና በተቀመጠው ቀን በመሄድ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል።
የሕክምና፣ የትራንስፖርት፣ ምግብ እና ማረፊያ ወጭዎች በነፃ የሚሸፈን ይኾናል። ከ600 በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችም አገልግሎቱን ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።