ወላጆች በጽኑ ቢታመሙ፣ በሞት ሲለዩ፣ በሱስ: በአለመግባባትና መሰል ጉዳዮች ቤተሰቡን ማስተዳደር ሲሳናቸው እና በመሳሰሉ ምክንያቶች ልጆች የወላጅን ሚና ተክተው ቤተሰብን እንዲያስተዳድሩ ሊገደዱ ይችላሉ::

▫️ይህ ጉዳይ በሃገራችን በስፋት ይስተዋላል:: በተለይም የመጀመርያ ልጆች ታናናሾቻቸውን ልክ እንደ ወላጅ ሁነው እንዲያሳድጉ ሃላፊነት ሲወስዱ ማየት የተለመደ ነገር ነው:: ታናናሾቻቸውን ለማሳደግ ራሳቸውን መስዋዕት ያደረጉ ብዙ አሉ::

እነዚህን ሃላፊነቶች በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን:-

  • Instrumental/ቁሳዊ/ parentification- ይህ ልጆች የቤተሰብን ቁሳዊ/አካላዊ ፍላጎት እንዲያሟሉ ሃላፊነት ሲጣልባቸው ነው:: ለቤተሰቡ ምግብን ማቅረብ: ስራ ሰርቶ ገቢ ማስገኘት: የቤተሰብ ቢዝነሶችን ማሳለጥ እና የመሳሰሉ ጉዳዮችን እንዲከውኑ ይጠበቅባቸዋል::
  • Emotional Parentification- ይህ ደግሞ ለቤተሰቡ ስነልቦናዊና እና የስሜት ድጋፍን የመስጠት ሃላፊነት የተጣለባቸውን ይመለከታል::

ስነልቦናዊና ማህበራዊ ዳራው ምን ይመስላል?

  • ይህን ሃላፊነት በተለይም ከአፍላነታቸው ጀምረው የተሸከሙት እንደሆነ: እንደየእድሜያቸው የሚጠበቀውን ስነልቦናዊና ማህበራዊ የእድገት ደረጃዎች(psychosocial development) እንዳያሳኩ እንቅፋት ሊሆንባቸውና ለተለያዩ ስነልቦናዊና ማህበራዊ ቀውሶች ሊያጋልጣቸው ይችላል::
  • በእድሜያቸው አለመብሰል ምክንያት አስቸጋሪ አጋጣሚዎችን የመቋቋምያ መንገዶቻቸው(coping) በደምብ የዳበሩ አለመሆኑ ለችግር ተጋላጭነታቸውን ይጨምረዋል:: ነገሮችን በጥልቀት እንድንመዝን እና እንድናገናዝብ የሚያደረገው የአንጎላችን ክፍል( Prefrontal cortex) ስራውን በደምብ መከወን የሚጀምረው በሃያዎቹ እድሜያችን ገደማ እንደሆነ ይታመናል:: አንዳንድ ቀድመው የሚበስሉ(early matures) እንዳሉ ሁነው::
  • በትምህርት አለመግፋት፣ በኢኮኖሚ አለመደርጀት፣ ለጭንቀት: ለድብርት ህመም ፣ ለአጽ ተጠቃሚነት: የስብዕና መዛነፍና ለመሳሰሉ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ችግሮች የሚጋለጡት ብዙ ናቸው::
  • ደግሞም በሌላ አንጻር ቤተሰብ በመምራት ሂደት የሚኖራቸው ተሞክሮ መልካም ከሆነ: በራስ መተማመናቸው የዳበረ እና ችግሮችን የመቋቋም እና የመፍታት ችሎታቸው የተሻለ ሊሆን ይችላል:: Internal locus of control ይኖራቸዋል::
    **

አሻም!

ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት

https://www.facebook.com/DrEstif
https://t.me/DrEstif

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *